የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት በቅርቡ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉትን የ20/80 እና የ40/60 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለሚዲያ ባለሙያዎች አስጎብኝቷል፡፡ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በተደረገው በዚሁ ጉብኝት በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች በርካታ ግንባታዎች እየተካሄዱ መሆኑን አይተናል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 20/80 በብዛት የሚገኝበት የኮዬ ፈጬ ሳይት አንዱ ነው፡፡ ይህ ሳይት በቅርቡ ለባለ ዕድለኞች ይተላለፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ አሥር ሺሕ 20/80 ቤቶችን ይዟል፡፡ ሌላው ከሰባት ሺሕ በላይ 40/60 ኮንዶሚኒየሞች የሚገኙበት ደግሞ የአያት አካባቢ ነው፡፡ ሁሉም ግንባታቸው ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ጽሕፈት ቤቱ የገለጸ ሲሆን፣ የመሠረተ ልማት አቅርቦት በተለይ መብራት እየተንተጓተ እንደሚገኝም ጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት

1178total visits,1visits today

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Facebook

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!
×

Like us on Facebook