The 12th round Condominium winners :

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2ሺ6ዐ5 ቤቶችን ለእድለኞች በእጣ አስተላለፈ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2ዐ/80 የቤት መርሀ ግብር የተገነቡ 2ሺ 6ዐ5 ቤቶችን ለእድለኞች በእጣ አስተላለፈ፡፡ ዛሬ እጣ የወጣባቸውን ቤቶች ጨምሮ ለእድለኞች የተላለፉ ቤቶች ወደ 178ሺ ከፍ ብሏል፡፡ በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ እንደገለፁት በ1997 ዓ.ም በባለ3 መኝታ የተመዘገቡ የከተማዋ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ በዚህ ዙር የቤት ባለቤት ሆነዋል፡፡ ዛሬ በተካሄደው 12ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ባለእድል የሆኑ የከተማ ነዋሪዎች በ1 ወር ጊዜ ውጥ የቁልፍ ርክክብ የሚደረግላቸው ሲሆን የቤት ዋጋውም በ11ኛው ዙር ለባለ እድለኞች በተላለፈበት ዋጋ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ በመገንባት ላይ ያለውን ከ94 ሺ በላይ ቤቶች በሚቀጥለው ዓመት አጠናቅቆ ለቤት ባለ ዕድሎ ለማስተላለፍ እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡.

 

STUDIO

SINGLE BED ROOM

DOUBLE BED ROOMS

THREE BED ROOMS

 

To Search  the list of winners Click here

3656total visits,1visits today

Facebook

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!