#ለ2ዙር #የ40_60_ባለእድለኞች

 

#የ40_60 መኖሪያ ቤቶችን የማስተላለፍ ስራ በያዝነው ሳምንት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። ስለሆነም ለመረከብ የሚያስፈልገው ማስረጃዎች፦

.

  1. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
  2. የጋብቻ ምስክር ወረቀት/ 6ወር ያላለፈው ያላገባ የምስክር ወረቀት
  3. በራሶ ስም ቤት የሌላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ከሚኖሩበት ወረዳ የተሰጠ ማረጋገጫ፤

.

  1. ሁሉም የቤት እድለኛ ቤቱን ለመረከብ ውል ሲዋዋሉ በአዲሱ የዋጋ ተመን መሰረት የቤቱን 40% በቅድሚያ መክፈል ይጠበቃል

 

  1. ውጭ ሀገር ያላችው እድለኞች ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ/ቆንስላ የእርሶን አንድ ጉርድ ፎቶ እና ውክልና የምትሰጡትን ሰው ሙሉ ስም፤ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በመጥቀስ፤ ውሉላይ በግልጽ የሚወከለው ሰው የደሮሶትን ቤት “እንደእኔ ሆኖ እንዲዋዋልልኝ” የሚል መጠቀስ ይኖርበታል።

.

 

በቅድሚያ በቦሌ ክ/ከተማ በሚገኘው ለዚሁ ስራ ከተደራጀው ቢሮ ቅፅ 03 እና 09 የተባሉ መረጃዎችን በመውሰድ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለወረዳ የምታደርሱ ይሆናል። ከዛም ከባንክና ከወረዳው መረጃውን አጠናቃችሁ ስትቀርቡ ውል መዋዋል ትችላላችሁ።

.

ስራውን የሚያከናውነው መገናኛ ባለው በቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ፣ ከመሬት አስተዳደር ጀርባ ባለ አዳራሽ ስረኛው ክፍል ውስጥ የሚገኝ አዲስ የተደራጀ ቢሮ ነው።

 

በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተገንብተው በዕጣ ለመተላለፍ ዝግጁ የሆኑ የቤቶች ጠቅላላ የግንባታ፣ የመሠረተ ልማት እና የመሬት ሊዝ ወጭ አማካይ የካሬ ሜትር ዋጋ 8,404.42 ብር ሲሆን መንግስት የመንገድ መሠረተ ልማት እና የመሬት የሊዝ ዋጋን ሙሉ በሙሉ ድጎማ በማድረግ የ2ኛው ዙር የማስተላለፊያ የካሬ ዋጋ 6922.14 ብር ይሆናል፡፡

For More

1790total visits,1visits today

Facebook

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!