ሐምሌ 3 2009 ዓም

ዕጣ የወጣባቸው በሰንጋ ተራና እና ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በሚገኙ 972፥ ባለ አራት፣ ባለሶስት እና ባለሁለት መኝታ ቤት እያንዳንዳቸው 324 ቤቶች ናቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ በተካሄደው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ በመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በተዘጋጀ ሶፍትዌር አማካኝነት ታዛቢዎች በተገኙበት የተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ፥ ባንኩ ለቤቶች ልማት ዘርፍ ስኬት የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አባታ ስጦታው በበኩላቸው፥ የተቀናጀ የቤቶች ልማት መርሃ ግብሩ የነዋሪዎችን የቤት ችግር ከመቅረፉ ባሻገር ምቹና ዘመናዊ የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር ማስቻሉን ገልጸዋል።

መንግስት ባካሄደው የቤቶች ልማት መርሃ ግብርም እስካሁን ከ175 ሺህ በላይ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተገንብተው መተላለፋቸውን አስታውሰዋል።

የቤቶች ልማት ዘርፍ ግንባታው በየአመቱ ከ60 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረ መሆኑንም ምክትል ከንቲባው አንስተዋል።

በተለይም ደግሞ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወገኖች የስራ እድልን ጨምሮ ሰፊ የገበያ ትስስር መፍጠሩንም ጠቅሰዋል።

ምክትል ከንቲባው አሁን ላይም ከ94 ሺህ በላይ የ20/80 እና ከ39 ሺህ በላይ ደግሞ የ40/60 ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አሁን በ40/60 እየተገነቡ ላሉ ቤቶችም የከተማ አስተዳደሩ 140 ሄክታር ከሊዝ ነጻ መሬት በማቅረብና በግንባታ ወቅት የሚስተዋሉ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር የተያያዙ ወጪዎችንና የመሰረተ ልማት ግንባታ ሸፍኗልም ነው ያሉት።

በዛሬው እለት ግንባታቸው ተጠናቆ ለባለ ዕድለኞች ዕጣ ለወጣባቸው ቤቶች ግንባታ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም በከተማ አስተዳደደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዛሬው እለት እጣ የወጣባቸው ቤቶች ባለ አራት መኝታ ቤት 168 ነጥብ 68 ካሬ ሜትር፣ ባለ ሶስት መኝታ 129 ነጥብ 5 ካሬ ሜትር እንዲሁም ባለ ሁለት መኝታ 124 ነጥብ 97 ካሬ ሜትር ስፋት አላቸው።

ዋጋቸውም በካሬ ሜትር 4 ሺህ 918 ብር ከ72 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

አጠቃላይ በ40/60 መርሃ ግብር ከተመዘገቡት መካከል 17 ሺህ 644ቱ ሙሉ በሙሉ ሲከፍሉ፥ 41 ሺህ 348 ደግሞ 40 በመቶና ከዚያ በላይ ከፍለዋል።

በዕጣው ከ18 ወራት በፊት መቶ በመቶ የቆጠቡ 11 ሺህ 88 ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን፥ በዚህኛው ዕጣ ለባለአንድ መኝታ የተመዘገቡ ቆጣቢዎች አልተካተቱም፡፡

አሁን ዕጣ በሚወጣባቸው ቤቶች ላይ መንግስት ለግንባታ ወጪያቸው 725 ሚሊየን ብር ድጎማ ማድረጉ ተጠቁሟል።

ለመኖሪያ ቤት ዕጣ ከሚወጣባቸው በተጨማሪም 320 የንግድ ቤቶች በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተዘጋጁ ሲሆን፥ ቤቶቹ በካሬ ሜትር 17 ሺህ ብር በሆነ የመነሻ ዋጋ የሽያጭ ጨረታ ይወጣባቸዋል።

 

የስም ዝርዝሩ ለማየት winners list ይጫኑ

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጣ

5111total visits,1visits today

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Facebook

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!
×

Like us on Facebook