ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍ/ብሄር ችሎት፤ የከሳሽን (98 ከሳሾች) የተሻሻለ ክስ አዳምጧል።
.
#የክስ_ማሻሻያ፦ “100℅ ለቆጠቡ ቅድሚያ ይሰጥ የሚለውን የቀድሞ ክስ በማሻሻል የቤቱን ዋጋ አሁን ያለውን ዋጋ 40% የቆጠቡ ማለትም የምዝገባ ግዜ ያለውን 100% የቆጠቡ ብቻ ናቸው እጣ ውስጥ መግባት የነበረባቸው በሚል ባለ 6ገጽ የክስ ማሻሻያ እና 4ገጽ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ ዛሬ አቅርቧል።
.
በሌላ በኩል ግንቦት 21/2011 #በሪፖርተር_ጋዜጣ በወጣው ዘገባ https://www.ethiopianreporter.com/article/15762 “የፍርድ ቤቱን ተአማኒነት በሚያጎድፍ መልኩ የተዛባ ዘገባ አቅርቧል” በሚል ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው ላይ ማብራሪያ እንዲያቀርብ ችሎቱ ለዛሬ ያዘዘ ቢሆንም ሪፖርተር ጋዜጣ ችሎት ዛሬ አልቀረበም። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ለሰኔ 11/2011 እንዲቀርብ እና በዘገባው ላይ ማብራሪያ እንዲያቀርብ በድጋሚ ትዕዛዝ ሰቷል።
.
ተከሳሾች እና ጣልቃ የገቡ 61 የቤት እድለኞች ደግሞ በጉዳዩ ላይ ለሰኔ 11 መልስ እንዲያቀርቡ እና ሰኔ 18/2011 ለክርክር እንዲቀርቡ ችሎቱ ቀጥሯል።

የ40/60 የችሎት ውሎ

1309total visits,2visits today

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Facebook

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!
×

Like us on Facebook