ለዕጣው ዝግጁ የሆኑ ቤቶች ብዛት 972 ሲሆኑ፥ ባለ አራት፣ ባለሶስት እና ባለሁለት መኝታ ቤት እያንዳንዳቸው 324 ቤቶች ለዕጣ ዝግጁ ሆነዋል።

ቤቶቹ ባለ አራት መኝታ ቤት 168 ነጥብ 68 ካሬ ሜትር፣ ባለ ሶስት መኝታ 129 ነጥብ 5 ካሬ ሜትር እንዲሁም ባለ ሁለት መኝታ 124 ነጥብ 97 ካሬ ሜትር ስፋት አላቸው።
ዋጋቸውም በካሬ ሜትር 4 ሺህ 918 ብር ከ72 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህ መሰረት ባለ አራት መኝታ ቤት 829 ሺህ 689 ብር ከ69 ሳንቲም፣ ባለ ሶስት መኝታ ቤት 636 ሺህ 974 ብር ከ24 ሳንቲም እንዲሁም ባለ ሁለት መኝታ ቤት 614 ሺህ 692 ብር ከ43 ሳንቲም ዋጋ አላቸው።

በቅዳሜው ዕጣ ከ18 ወራት በፊት መቶ በመቶ የቆጠቡ 11 ሺህ 88 ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን፥ በዚህኛው ዕጣ ለባለአንድ መኝታ የተመዘገቡ ቆጣቢዎች አልተካተቱም፡፡

ባለአራት መኝታ ቤት ከዕጣው ውጭ ስለሆነ ባለ ሶስት መኝታ ላይ የሚሳተፉ ሰዎች አቅሙ ካላቸው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን፥ ይህ ካልሆነ ግን መንግስት የቤቶቹን የዋጋ ተመን ከፍሎ ይረከባል ተብሏል፡፡

በዚህ የዕጣ ስነ ስርዓት በእያንዳንዱ ፕሮግራም 20 ሰዎች በተጠባባቂ እጣ ይያዛሉም ነው የተባለው፡፡

በእጣው ውስጥ የመንግስት ሰራተኛ ሆነው 100 ፐርሰንት የቆጠቡ 20 በመቶ ቅድሚያ እድል ሲኖራቸው፥ ዲያስፖራዎች  እጣ ከሚወጣባቸው መካከል በ3 በመቶ ቤቶች ላይ ብቻ ይሳተፋሉ፡፡።

ከዚህ ውጭ ሁሉም ዕድለኞች በዕጣው ቀሪውን 77 በመቶ እኩል የሚሳተፉ ይሆናል።

እሁን ዕጣ በሚወጣባቸው ቤቶች ላይ መንግስት ለግንባታ ወጪያቸው 725 ሚሊየን ብር ድጎማ ማድረጉ ተጠቁሟል።

ለመኖሪያ ቤት ዕጣ ከሚወጣባቸው በተጨማሪም 300 የንግድ ቤቶች በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተዘጋጁ ሲሆን፥ ቤቶቹ በካሬ ሜትር 17 ሺህ ብር በሆነ የመነሻ ዋጋ የሽያጭ ጨረታ ይወጣባቸዋል።

 

Source: Fana BC

በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ የሚካተቱ ተመዝጋቢዎች እና የቤቶቹ ዋጋ ይፋ ሆነ

3399total visits,1visits today

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Facebook

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!
×

Like us on Facebook