የ40/60 የቁጠባ መኖሪያ ቤቶች ልማት ፕሮግራም የቅድሚያ አወሳሰንና የቤት ማስተላለፍ ስርዓት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 21/2005 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:

1.የተጠናቀቁ ቤቶችን ከቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በመረከብ በቁጠባ ብድር ስርዓቱ መሠረት የቁጠባ ግዴታቸውን ላሟሉና ቤቱን ለሚረከቡ ተጠቃሚዎች ከቤቱ ዋጋ እስከ 60 በመቶ የሚደርስ ብድር ቤቱን በዋስትና ይዞ እስከ 17ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ብድር ያበድራል፣
2.ወቅታዊ በሆነ መልኩ የመኖሪያ ቤቱን ዋጋ 40% እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ ደንበኞች ለብድር ብቁ መሆናቸው በባንኩ ይለያሉ፣
3.መስፈርቱን ያሟሉና የሚፈለግባቸውን የ40 በመቶ ወይንም ከዚያ በላይ ቁጠባ ያጠናቀቁ ተጠቃሚዎች ዝርዝር ለቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ያሳውቃል፣
4.ከዚህ በተጨማሪ ባንኩ ደንበኞች በደረሳቸው የመኖሪያ ቤት ህንጻ የወለልና ቤት ቁጥሩን በዕጣ ይለያል፣ በውሉ መሰረት ያስረክባል፣
5.ለብድር ብቁ ከሆኑ ደንበኞች መካከል የመኖሪያ ቤቱን ዋጋ 100% ተቀማጭ ያደረጉ ቅድሚያ የሚያገኙ ሲሆን ከከፍተኛው ወደ ዝቅተኛው አስቀማጭ እንደቅደም ተከተላቸው የሚፈጸም ይሆናል፣
6.በዚሁ መሰረት የቤት ድልድል ቅደም ተከተሉ በደንበኞች የቁጠባ መጠን ልክ፣ በምዝገባ ጊዜና በዕጣ ይሆንና ለብድር ብቁ የሆኑና ከፍተኛ ገንዘብ የቆጠቡ ቅድሚያ ዕድል ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን ለብድር ብቁ የሆኑ ደንበኞች በተለያዩ ምክንያቶች መኖሪያ ቤቶችን ማግኘት ባይችሉ የቁጠባ ሂሳቡ የሚቀጥል ይሆናል፣
7.ግንባታቸው የተጠናቀቁ ህንጻዎችን እንደተረከበ የ5 ዓመት የቁጠባ ውል ዘመኑን ሳይጠብቅ የሚፈለግባቸውን የ40 በመቶ ወይንም ከዚያ በላይ ቁጠባ ያጠናቀቁ ተጠቃሚዎችን እንደተቀማጭ መጠናቸው 100 በመቶ ቀጥሎ ወደታች በሚኖረው ቅደም ተከተል መሠረት የብድር ውል ይፈራረማል፣ የመኖሪያ ቤቱንም ያስረክባል፣

የቤት ሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ

ቤት የደረሰው እድለኛ ስሙ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ በኋላ ቀርቦ ውል እንዲፈጽም በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቀርቦ መዋዋል ይኖርበታል፡፡ የመጨረሻው ወይም 60ኛው ቀን በአል ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እንደ መጨረሻ ቀን ይወሰዳል፡፡ በዚህ አንቀጽ «ሀ» ቀርቦ ያልተዋዋለ ተጠቃሚ በራሱ ፈቃድ የቤት ሽያጭ እድሉን እንደተወው ይቆጠራል፥ ቤቶቹም ዳግም እጣ እንዲወጣባቸው ይደረጋል፡፡ በዚህ አንቀጽ «ለ» መሰረት ዳግም እጣ እንዲወጣባቸው የተለዩ ቤቶችን ለተጠቃሚው እስኪያስረክብ ድረስ ለቤቶቹ አጠባበቅ አስተዳደር ኤጀንሲው ሀላፊነት አለበት፡፡

የቤት ርክክብ ጊዜ ገደብ

ቤት የደረሰው እድለኛ ቤቱን እንዲረከብ ጥሪ ከተደረገለት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ቤቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ቤቱን መረከብ ካልቻለ ቤቱን ባለመረከቡ ምክንያት በቤቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳትም ሆነ ኪሳራ ኀላፊነቱ የግሉ ይሆናል፡፡

የቤት ሽያጭ ውል ስለማፍረስ

በራሱ ወይም በትዳር ጓደኛው ስም በከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ መስሪያ ቦታ እያለው ወይም ከዚህ በፊት ኖሮት በሽያጭ ወይም በስጦታ ለሶስተኛ ወገን መብቱን ያስተላለፈ ወይም ከዚህ በፊት የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ ተጠቃሚ የሆነ ወይም ለልማት ተነሺ ሆኖ የኮንዶሚኒየም ቤት የገዛ መሆኑ ከተረጋገጠ፡ ኤጀንሲው በሚሰጠው የማስተካከያ ማስጠንቀቂያ መሰረት ለማስተካከል ፈቃደኛ ሆኖ ካልተገኘ፣ በራሱ ፈቃድ ውሉ እንዲሰረዝ ወይም እንዲቋረጥ ከጠየቀ፣ በእጣ የወጣለት የቤት አይነት፣ የክፍል ብዛት እና የቦታው ስፋት ልኬት ላይ ቅሬታ ካለው እና በተቀመጠው የርክክብ ጊዜ ገደብ ቀርቦ ቤቱን ለመረከብ ፍቃደኛ ካልሆነ፣ ተጠቃሚው የካርታ እዳና እገዳ ተዘጋጅቶለት የብድር ውል ቀርቦ ካልፈረመ፣ ወርሀዊ የብድር ክፍያውን ለሶስት ተከታታይ ወራት ወይንም በአንድ አመት ውስጥ በድምሩ ለስድስት ጊዜ ወርሀዊ ክፍያ ካልፈጸመ የገዛውን ቤት አምስት አመት ሳይሞላው በሽያጭ ወይም በስጦታ ካስተላለፈ፣ የገዛውን ቤት በተረከበ በ30 ቀን ውስጥ የተከራየውን የመንግስት ቤት ለሚያስተዳድረው አካል ካላስረከበ፣ ከኤጀንሲው የገዛውን ወይም የተከራየውን ቤት ከተፈቀደው አላማ ወይም አገልግሎት ውጭ እየተጠቀመ ከሆነ፣

በዚህ መመሪያ መሰረት የተቀመጠውን ግዴታና ክልከላ በመተላለፍ ሀሰተኛ መረጃ አቅርቦ የቤት ሽያጭ ውል የተዋዋለ ከሆነ ውሉ ይፈርሳል፡፡

1938total visits,4visits today

Facebook

ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ለዘላለሙ!!
×

Like us on Facebook